ለተከበራችሁ የሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች፤ የ32ኛ መደበኛ እና 16ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔዎች የስብሰባ ጥሪ
በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 366(1)፣ 367(1)፣ 370፣371 እና 372 እንዲሁም በአክሲዮን ማኅበሩ በተሻሻለው የመመሥረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 18 መሠረት፣ የሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 32ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 16ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ፤ ሐሙስ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ቦሌ- አፍሪካ ጎዳና ላይ በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል አዳራሽ ውስጥ ስለሚካሄድ የኩባንያው ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በጉባዔው ላይ እንዲገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል::
1. አክሲዮን ማኅበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች| 1.1. የአክሲዮን ማኅበሩ ስም | ሕብረት ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር |
| 1.2. የአክሲዮን ማኅበሩ ዓይነት | በመድን ሥራ ላይ የተሠማራ ኩባንያ |
| 1.3. የአክሲዮን ማኅበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ /ካፒታል/ | ብር 2,000,000,000 |
| 1.4. የአክሲዮን ማኅበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ /ካፒታል/ | ብር 1,877,003,163.82 |
| 1.5. የአክሲዮን ማኅበሩ የምዝገባ ቁጥር | MT/AA/3/0052572/2014 |
| 1.6. የአክሲዮን ማኅበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻ | አዲስ አበባ፣ አራዳ ክ/ከተማ፣ወረዳ 01፣ የቤት ቁጥር 220 |
| 1.7. የአክሲዮን ማኅበሩ ድረ-ገጽ | https://www.hibretinsurance.com |
2. የባለአክሲዮኖች 32ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
2.1. የመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎችን ማጽደቅ፤
2.2. አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበልና የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅ፤
2.3. እ.ኤ.አ. የ2025/2026 የሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርትን ማድመጥ፤
2.4. እ.ኤ.አ. የ2025/2026 የሒሳብ ዓመት የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማድመጥ፤
2.5. በተራ ቁጥር 2.3 ላይ በቀረበው የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
2.6. በተራ ቁጥር 2.4 ላይ በቀረበው የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
2.7. እ.ኤ.አ. የ2025/2026 የሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈል ላይ በሚቀርበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
2.8. እ.ኤ.አ. የ2025/2026 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ዓመታዊ የሥራ ዋጋ መወሰን እና እ.ኤ.አ. የ2026/2027 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ወርሃዊ የአበል ክፍያ መወሰን፤
2.9. የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባላትን ምርጫ ማካሄድ እና ወርሀዊ አበላቸዉን ማስወሰን፡፡
3. የባለአክሲዮኖች 16ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች3.1. የአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎችን ማጽደቅ፤
3.2. የአክሲዮን ማኅበሩን የመመስረቻ ጽሑፍ ማሻሻል፤
3.3. የጉርሻ አክሲዮኖችን (Bonus Shares) በተመለከተ ተወያይቶ መወሰን፡፡
4. ማሳሰቢያ:
4.1. በጉባዔው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻቸው ሥልጣን ባለው የመንግሥት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ሠነድ ዋናውን እና አንድ ቅጂ በመያዝ ወይም በንግድ ሕግ አንቀጽ 377 መሠረት ጉባዔው ከመካሄዱ ከሦስት የሥራ ቀናት በፊት ፒያሳ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው የሕብረት ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር ዋና መ/ቤት 9ኛ ፎቅ አክሲዮን አስተዳደር ክፍል ለዚሁ ዓላማ በማህበሩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ ሞልተው በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባዔው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ ሆኖም፤ አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በማናቸውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን፣ እንዲሁም የኩባንያው ሠራተኞች ለባለአክሲዮኖች ወኪል በመሆን በጉባዔዎቹ ላይ መሳተፍ የማይችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፤
4.2. የአክሲዮን ማኅበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ፤ ዜግነታቸዉ ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያሳይ የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ወይም የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ዋናውንና ኮፒ በመያዝ በጉባዔው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው የማኅበሩ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው በትህትና እያስታወቅን፤
1.3 በተጨማሪም፤ የተሻሻሉትን የመመስረቻ ጽሁፍ አንቀጾችንና ሌሎች መረጃዎችን ከድርጅቱ ድረ-ገጽ፤ https://www.hibretinsurance.com ላይ መመልከት እንደሚቻል በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡ሕብረት ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ

